ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም ለተሳካ የኮፕ 32 ዝግጅት በጋራ  ይሰራሉ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 11/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም ለኮፕ 32 ዝግጅት ስኬት በትብብር እንደሚሰሩ አስታወቁ።

31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን ከዩናይትድ ኪንግደም የኢነርጂ ደህንነትና የኔት-ዜሮ (Net Zero) ሚኒስትር ሚያታ ፋንቡሌህ (ዶ/ር) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ እየጨመሩ ያሉ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች እና ተጨባጭ ውጤቶችን የሚያስገኝ ጠንካራ የአፈጻጸም ሂደት አስፈላጊነት ተነስቷል።

በተጨማሪም ለተሳካ የኮፕ 32 ዝግጅት፣ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እና በዩናይትድ ኪንግደም ቀጣይ የቡድን 20 (G20) ፕሬዚዳንትነት ወቅት በቅርበት ለመስራት ተስማምተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም