ኢትዮጵያ በኮፕ 32 የሁሉንም ወገኖች ቅድሚያ የሚያንጸባርቅ ግልጽና አካታች ሂደት ለማስፈን ቁርጠኛ ናት - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በኮፕ 32 የሁሉንም ወገኖች ቅድሚያ የሚያንጸባርቅ ግልጽና አካታች ሂደት ለማስፈን ቁርጠኛ ናት
አዲስ አበባ፤ ህዳር 11 /2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በኮፕ 32 የሁሉንም ወገኖች ቅድሚያ የሚያንጸባርቅ ግልጽና አካታች ሂደት ለማስፈን ቁርጠኛ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ገለጹ።
31ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በቱርኪዬ አንታሊያ መካሄዱን ቀጥሏል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከአነስተኛ ደሴት ሀገራት ጥምረት (Alliance of Small Island States - AOSIS) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
ጥምረቱ ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ፕሬዚዳንትነትን በመረከቧ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በቅርብ ትብብር ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሁሉንም ተዋዋይ ወገኖችና የድርድር ቡድኖች ቅድሚያ የሚያንፀባርቅ፣ ግልጽና አካታች የሆነ ሂደት ለማስፈን እንዲሁም የባለብዙ ወገን ድርድር ሂደቱን ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ውይይቱም ከአንታልያ እስከ አዲስ አበባ የሚዘልቅ ጠንካራ አጋርነት እና ቀጣይነት ያለው ትብብር ለማረጋገጥ ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት አንፀባርቋል።