ቀጥታ፡

የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 11/2019 (ኢዜአ) ፦ አራተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ስነ ስርዓት በዩጋንዳ ካምፓላ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የዩጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮቢናህ ናባንጃ፣ የኢጋድ ከፍተኛ አመራሮች፣ተሸላሚ ጋዜጠኞች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

ሽልማቱ በቀጣናው ላይ በሚገኙ ሀገራት ከፍልሰተኞች ጋር በሰሯቸው ስራዎች እውቅና የሚያገኙበት ነው።

ብሮድካስት፣ ህትመት፣ ፎቶግራፍ፣ ዲጂታል ሚዲያ፣ ሀገር በቀል ቋንቋዎች እና የእድሜ ልክ ተሸላሚ የሽልማት ዘርፎቹ ናቸው።

ይህም በቀጣናው ያለው የጋዜጠኝነት ስራ እና ልህቀት እውቅና የሚያገኝበት ነው ፐልስ ኦፍ አፍሪካ አራተኛውን የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ስነ ስርዓት በቀጥታ እያስተላለፈ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም