ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 11/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አማኑኤል ኤርቦ እና የሀዲያ ሆሳዕናው ዳግም ወንድሙ በራሱ ላይ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ቅዱስ ጊዮርጊስ በዘጠኝ ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
በሊጉ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሀዲያ ሆሳዕና በአራት ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቻል ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
መቻል በ11 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ሶስት ተስተካካይ ጨዋታዎች የሚቀሩት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሁለት ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።