የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2027 APEX ባለአምስት ኮከብና የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ዕውቅና ተቀዳጀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2027 APEX ባለአምስት ኮከብና የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ዕውቅና ተቀዳጀ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 11/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2027 APEX ባለአምስት ኮከብ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ እንዲሁም የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ (Best Overall Airline in Africa) ዕውቅና ማግኘቱን አስታወቀ።
የተገኘው የዕውቅና ሽልማት አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ የበረራ መረቡ ላይ ለተሳፋሪዎች ምቹ፣ አስተማማኝ እና አስደሳች የጉዞ ተሞክሮዎችን ለማቅረብ ያለውን ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቁ መሆናቸውን ገልጿል።
አየር መንገዱ ደንበኞቹ አብረውት ስለሚጓዙና የስኬቱ አካል በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናውን ማቅረቡን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።