ኢትዮጵያ እና ጣልያን ለተሳካ የኮፕ 32 ጉባኤ ዝግጅት ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ጣልያን ለተሳካ የኮፕ 32 ጉባኤ ዝግጅት ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 10/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ጣልያን ለተሳካ የኮፕ 32 ጉባኤ ዝግጅት ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።
31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል።
የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን፣ ከጣልያን የአካባቢና የኢነርጂ ደህንነት ሚኒስትር ጊልቤርቶ ፒኬቶ ፍራቲን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያና በጣልያን መካከል ባለው ዘላቂ ወዳጅነትና ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ በመመስረት፣ ለአየር ንብረት ርምጃ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
ለተሳካ ኮፕ 32 ዝግጅት ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከርም ተስማምተዋል።