ቀጥታ፡

የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ከCOP31 የድርድር ፕሬዚዳንት ክሪስ ቦወን ጋር ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 10/2019(ኢዜአ)፦ በCOP 31 እና COP 32 ፕሬዚዳንትነት መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር፣ የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ከCOP31 የድርድር ፕሬዚዳንት ክሪስ ቦወን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንቱ ጌዲዎን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር)፣ የCOP31 ፕሬዚዳንትነት በድርድሩ ያሳየውን አመራር በማድነቅ ግልጽና አካታች ሂደቱን፣ የመጀመሪያውን ውሳኔ (cover decision) ረቂቅ በቅድሚያ መለቀቁን እና እስካሁን የተመዘገበውን ውጤት አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ ለተሳካ ውጤት ያላትን ድጋፍ በድጋሚ በማረጋገጥ፣ COP31 ለCOP32 መሰረት የሚሆን ጠንካራና ግልጽ ውጤት ይዞ እንዲጠናቀቅ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

የCOP31 የድርድር ፕሬዚዳንት ክሪስ ቦወን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪፊኬሽን ትግበራ አጀንዳ ለሰጠችው ድጋፍ አመስግነው፣ ወደ ተጨባጭ ውጤቶች ለመቀየር ያላቸውን ቁርጠኝነት አስታውቀዋል።

በተጨማሪም አውስትራሊያ ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የተሳካ COP32 እንዲካሄድ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ማረጋገጣቸም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም