ቀጥታ፡

በክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍን ውጤታማ ለማድረግ የአቅም ግንባታ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው

መቀሌ፤ ህዳር 10/2019(ኢዜአ)፦ በትግራይ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍን ውጤታማ ለማድረግ የአቅም ግንባታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተመለከተ።

የትግራይ ክልል የፌደራል መንግስት ባለአደራ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የሠራተኞቹን የሥራ ብቃትና የሙያ ክህሎት ለማጎልበት ስልጠና እየሰጠ ነው።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ሀፍቱ ብርሀኑ በወቅቱ እንዳሉት በክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍን ውጤታማና ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።

አሁን ላይ የዘርፉን አፈጻጸም ለማሻሻል፣ የባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት እንዲሁም የአሰራር ብቃትን ለማሳደግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

ስልጠናው በተጨማሪም በከተማ ልማት እና በግንባታ ዘርፍ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑን አመልክተዋል።

በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ሊከናወኑ በሚገቡ ቁልፍ ተግባራትና የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ከቢሮው ሰራተኞች ጋር ውይይት መደረጉንም አውስተዋል።

በከተማ ልማት፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በኮንስትራክሽን ዘርፎች የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመፍታትና የዘርፉን አሰራር ውጤታማ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በምህንድስና እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ በቀጣይ ስድስት ወራት የሚሰሩ ስራዎች በተመለከተ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም