ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በኮፕ 32 ጉባኤ ሁሉንም ሀገራት በፍትሃዊነት ለማሳተፍ በቁርጠኝነት ትሰራለች -የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ህዳር 10/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በምታስተናግደው የኮፕ 32 ጉባኤ ሁሉንም ሀገራት ፍትሃዊ እድል እንዲያገኙ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ገለጹ።

31ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በቱርኪዬ አንታሊያ መካሄዱን ቀጥሏል።

ከጉባኤው ጎን ለጎን  ሁለተኛውን ዓለም አቀፍ የጋራ ግምገማ (Second Global Stocktake) ይፋ ለማድረግ የተዘጋጀ የሚኒስትሮች ከፍተኛ ደረጃ ውይይት ተካሄዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ትብብርን ለማጠናከር ያለመውን የኢትዮጵያን ርዕይ አብራርተዋል።

ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የጋራ ግምገማ፣ በጋራ የተመዘገበውን እድገት በግልጽ ሁኔታ መገምገም፣ የአፈጻጸም እንቅፋቶችን መለየት፣ እንዲሁም የአየር ንብረት እርምጃዎችንና ድጋፎችን ለማፋጠን የሚያስችሉ አማራጮችን ማመላከት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

በተጨማሪም በአዲስ አበባ በሚካሄደው የኮፕ 32 ጉባኤ ይህንን ሥራ ወደፊት ለማስቀጠልና ሁሉም ሀገራት ትርጉም ያለው ድምፅ እንዲኖራቸውና የድርሻቸውን ለመወጣት ፍትሐዊ ዕድል እንዲያገኙ ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም