አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር - ኢዜአ አማርኛ
አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር
)አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንና ለስራቸው ክብር መስጠት ተገቢ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
በአዲስ አበባ 57 ሄክታር የሚሸፍን አዲስ የኮሪደር ልማት ሥራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ተመርቋል።
ይህ ልማት፤ ከቦሌ መድኃኔዓለም በጎላጉል እስከ እንግሊዝ ኤምባሲ፣ ከቦሌ መድኃኔዓለም እስከ ሞኤንኮ፣ ከቦሌ ትምህርት ቤት እስከ አደይ አበባ ሞዴል መንደር፣ ከኢምፔሪያል ሆቴል እስከ ሻላ ፓርክ፣ ከቺቺኒያ እስከ ቦሌ ሩዋንዳ፣ ከአደይ አበባ ስታዲየም እስከ ቦሌ መንገድ እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን የሚያካትት ነው።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ጎን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አባት ለሆኑት ለአቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሀውልት እንደቆመላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ያደረጉት አስተዋጽኦ ትልቅ እና የሚታወቅ በመሆኑ፣ ለሳቸው የሚገባውን ክብር መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል።
እሳቸውን ማስታወስ መቻሉ ትልቅ ነገር እንደሆነና ለኢትዮጵያ ሰርተው ያገለገሉ ሰዎች እንዳይዘነጉ ምልክታቸውን በማስቀመጥ የሀገር ስም ማስተዋወቅ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል።
በተጨማሪም ትልቅ ሰው መሆናቸውና የሚገባቸው ክብር እንዲሰጥ ማስታወስ መቻሉ ትልቅ ነገር እንደሆነም ገልጸዋል።