ቀጥታ፡

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን መከበሩ አብሮነትንና አገራዊ መግባባትን ለማጠናከር እያገዘ ነው- የአፋር ክልል ምክር ቤት

ሠመራ፣ህዳር 9/2019(ኢዜአ)፦  የብሔር ብሔረሰቦች ቀን መከበር አብሮነትንና አገራዊ መግባባትን በማጠናከር ረገድ የጎላ ሚና እያበረከተ መሆኑን የአፋር ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ፋጡማ መሐመድ ተናገሩ።

አፈ ጉባዔ ፋጡማ መሐመድ  21ኛ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአፋር ክልል ደረጃ የሚኖረውን አከባበር አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች አካላት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመሆን ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውን፣ ማንነታቸውን እና እሴቶቻቸውን በጋራ የሚያስተዋውቁበት መድረክ ነው ብለዋል።

በዓሉ መከበሩ  የጋራ ትርክቶችን ለማስረጽ፣ አንድነት ለማጠናከር እንዲም ሕብረ ብሔራዊነትን ለማጠናክር እንዳስቻለ ነው ያመለከቱት። 

ሕገ መንግሥቱ የጸደቀበት ይህ ቀን እጅግ ውጤታማ ለሆኑ አገራዊ ስኬቶች በር የከፈተ መሆኑንም አንስተዋል።

አገራዊ መረጋጋትን ለማጠናከርና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን አጎልብቶ  ለመጓዝ ና ሕብረ ብሔራዊ እኩልነትን ለማሳደግ የራሱ የሆን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም አስረድተዋል።

በዓሉን በክልሉ የተለያዩ ዞኖች እና ከአጎራባች ክልሎች ጋር በመቀናጀት በድምቀት እንደሚከበርም ነው አፈጉባዔዋ በዚሁ ወቅት የተናገሩት።

በዓሉን የተለያዮ ተቋማት አንድ ላይ በመሆን የሚያከብሩት ሲሆን  ሲምፓዚየሞችና ሌሎች ዝግጅቶችም እንደሚኖሩ ነው ያብራሩት።

በዘንድሮው ዓመት የሚከበረው 21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን "በብዝኃነት የደመቀች በምክክር የፀናች ሥልጡን ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሀሳብ ሕዳር 29 ቀን 2019 ዓም በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ ይከበራል

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም