አቶ አደም ፋራህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አዲሱ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
አቶ አደም ፋራህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አዲሱ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በመረጃው፣ አቶ አደም ፋራህ የአየር መንገዱ አዲሱ የቦርድ ሊቀመንበር በመሆናቸው የተሰማውን ከፍተኛ ደስታና አክብሮት ገልጿል።
አየር መንገዱ አክሎም አዲሱ ሊቀመንበር ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ቤተሰብ በደህና መጡ በማለት አቀባበል ያደረገ ሲሆን በቀጣይ የኃላፊነት ጊዜያቸው መልካምና የተሳካ የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝቷል።