በመቀሌ ከተማ የተባበሩት መንግሥታት ልዑካንና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ከሃይማኖት አባቶች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በመቀሌ ከተማ የተባበሩት መንግሥታት ልዑካንና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ከሃይማኖት አባቶች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019 (ኢዜአ)፦ የተባበሩት መንግሥታት ልዑካንና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በመቀሌ ከተማ ከሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል።
ልዑካኑ ከትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር አመራሮች ጋር ውይይት ካካሄዱ በኋላ ከሃይማኖት አባቶቹ ጋር የተወያዩ ሲሆን፣ ውይይቱ በክልሉ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታና የተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮችን የተመለከተ ነው።
ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በመቀሌ ከተማ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያካሄዱ የሚገኙት ልዑካኑ፣ በቆይታቸው ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር እንደሚወያዩ ተገልጿል።
ጉብኝቱ በክልሉ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለመረዳትና በክልሉ ባሉ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ያለመ እንደሆነም ነው የተጠቀሰው።