ቀጥታ፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑካን እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች መቀሌ ገቡ

‎አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019(ኢዜአ)፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑካን እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ለስራ ጉብኝት መቀሌ መግባታቸው ተገለጸ።

ልዑካኑ በአሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች እና የመቀሌ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) እና ሌሎች የባለአደራ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

‎‎የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልኡካን ከዛሬ ኅዳር 8 ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ኦፊሴላዊ የሥራ ጉብኝት በመቀሌ ከተማ ያካሂዳሉ።

‎‎ልዑካኑ ከትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ ከሐይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

‎‎ሰብአዊ ዕርዳታ፣ ተፈናቃዮች፣ የዲዲአር (የትጥቅ የማስፈታት፣የዲሞቢላይዜሽን እና የመልሶ ማቋቋም) ሂደት እንዲሁም የክልሉ ሰላም ጉዳይ ውይይት ከሚደረግባቸው ጉዳዮች መካከል መሆናቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም