ኮፕ 32 የአየር ንብረት ጥበቃ ርምጃዎችና ልማት በተቀናጀ መንገድ የሚተገበሩበት ወሳኝ የትብብር ዕድል ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኮፕ 32 የአየር ንብረት ጥበቃ ርምጃዎችና ልማት በተቀናጀ መንገድ የሚተገበሩበት ወሳኝ የትብብር ዕድል ነው
አዲስ አበባ፤ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ)፦ ኮፕ 32 የአየር ንብረት ጥበቃ ርምጃዎችና ልማት በተቀናጀ መንገድ የሚተገበሩበት ወሳኝ የትብብር ዕድል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ዋና ተደራዳሪ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ።
31ኛው የተባበሩት መንግስት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) እየተካሄደ ይገኛል።
የገንዘብ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ዋና ተደራዳሪ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን የተካሄደውን የዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ዘርፍ መሪዎች ጋር የውይይት መድረክ መርተዋል።
ውይይቱ ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ በአጋርነትና በድጋፍ ላይ ያተኮረ ነበር።
ሚኒስትሯ ኮፕ 32 ለብዙ ወገኖች ትብብር ወሳኝ ዕድል መሆኑንና የአየር ንብረት ጥበቃ ርምጃዎችና ልማት በተቀናጀ መንገድ ሊተገበሩ እንደሚችሉ አጉልተው ገልጸዋል።
ድጋፍ እያደረጉ ላሉ አጋሮች ምስጋና አቅርበው፣ የበጎ አድራጎት ዘርፉ ከጉባኤው ዝግጅት ባለፈ የድርድር ውጤቶችን ወደ ተግባራዊ እርምጃዎችና የኢንቨስትመንት ዕድሎች በመቀየር እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
የበጎ አድራጎት ዘርፍ መሪዎችም የኢትዮጵያን ቅድመ ዝግጅት በማድነቅ፣ ለኮፕ 32 ፕሬዚዳንትነት አመራር ድጋፍ ለማድረግና በትብብር ለመሳተፍ ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።