ቀጥታ፡

የአየር ንብረት ዕቅዶችን ከፋይናንስና ኢንቨስትመንት ጋር ማገናኘት ትግበራን ለማጠናከር ወሳኝ ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ)፦ የአየር ንብረት ዕቅዶችን ከፋይናንስና ኢንቨስትመንት ጋር ማገናኘት ትግበራን ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ዋና ተደራዳሪ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ።

31ኛው የተባበሩት መንግስት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) እየተካሄደ ይገኛል።

የገንዘብ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ዋና ተደራዳሪ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን፣ ሀገራት የአየር ንብረት ጥበቃ እርምጃ ቃል ኪዳኖቻቸውን በኢንቨስትመንት ሊደገፉ ወደሚችሉ ፕሮጀክቶችና ተጨባጭ ተግባራት ለመቀየር የሚያግዘውን የCOP31 ፕሬዚዳንሲ ውጤት የሆነውን “የአየር ንብረት ትግበራ ድልድይ” (Climate Implementation Bridge - BRIDGE) ይፋ የማድረግ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል።

በማስጀመሪያው ላይ ከ”BRIDGEዕ የመጀመሪያ ቡድን አባል ሀገራት የመጡ ሚኒስትሮች፣ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እንዲሁም የብዙ ወገን የልማት ባንኮች (multilateral development banks) ተወካዮች ተገኝተዋል።

ፕሮግራሙ ቅድሚያ ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮችና በጋራ ቁርጠኝነቶች ዙሪያ ስትራቴጂያዊ ውይይት አካሂደዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የሀገራትን የአየር ንብረትና የልማት ቅድሚያ ጉዳዮች ከፋይናንስ፣ ከኢንቨስትመንትና ከቴክኒክ ድጋፍ ጋር ማገናኘት ትግበራን ለማጠናከር ያለውን አስፈላጊነት አጉልተው ገልጸዋል።

አያይዘውም፣ ለኢትዮጵያ እንዲህ ያለው ትብብር በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ባለው የተልዕኮ ደረጃና በተግባራዊ አፈጻጸም መካከል ያለውን ክፍተት በማጥበብ፣ ብሔራዊ ዕቅዶችን ወደ ኢንቨስትመንት ዕድሎችና ተጨባጭ ውጤቶች ለመቀየር እንደሚረዳ አመልክተዋል።

ውይይቱ ከኮፕ 31 በኋላም የሀገራትን በትብብር የሚመራ አተገባበር ለማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ከአጋር አካላት ጋር ሐሳብ ለመለዋወጥ ዕድል ፈጥሯ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም