ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ከቀኑ 10 ሰዓት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀዋሳ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአራት ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ሀዋሳ ከተማ በአምስት ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በሶስተኛ ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ1 ለ 0 ሽንፈት ሲያስተናግድ ሀዋሳ ከተማ ከቦሌ ክፍለ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ሁለቱም ቡድኖች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታሉ።

በሌላኛው መርሐ ግብር ቦሌ ክፍለ ከተማ ከሲዳማ ቡና ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ቦሌ ክፍለ ከተማ በአራት ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። ሲዳማ ቡና በሶስት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

በሶስተኛ ሳምንት ቦሌ ክፍለ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ አንድ አቻ ሲለያይ ሲዳማ ቡና ይርጋጨፌ ቡናን 2 ለ 1 በመርታት የሊጉን የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት እስከ ነገ ይቆያል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዘጠኝ ነጥብ ሊጉን እየመራ ይገኛል።

የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ እጸነት ግርማ እና የመቻሏ ቱሪስት ለማ በተመሳሳይ ሶስት ግቦች እየመሩ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም