በወጣቶች ኦሊምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አቀባበል ተደረገለት - ኢዜአ አማርኛ
በወጣቶች ኦሊምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አቀባበል ተደረገለት
አዲስ አበባ፤ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ)፦ በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ሲገባ አቀባበል ተደረገለት።
ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ፡የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እና ሌሎች እንግዶች አቀባበል አድርገውለታል።
ቡድኑ በውድድሩ በአትሌቲክስ 5 ወርቅ እና 3 ብር በድምሩ 8 ሜዳልያዎች በማግኘት አጠናቋል።
ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ስፖርቶች አምስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
አትሌቲክስ፣ ውሹ፣ ቴኳንዶ፣ ብስክሌት እና ውሃ ዋና ኢትዮጵያ የተሳተፈችባቸው ስፖርቶች ናቸው።
ናትናኤል ክንፈ በውሹ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝቷል።