የመቐለ ከተማ አስተዳደር ለፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የክብርና የምስጋና ሽልማት አበረከተ - ኢዜአ አማርኛ
የመቐለ ከተማ አስተዳደር ለፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የክብርና የምስጋና ሽልማት አበረከተ
የመቐለ ከተማ ባለአደራ አስተዳደር የሀገር መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ሰላምን ለማረጋገጥ እየከፈለ ለሚገኘው ታላቅ መስዋዕትነት እውቅና በመስጠት፣ ለጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የምስጋና ሽልማት አበረከተ።
የመቐለ ከተማ ባለአደራ አስተዳደር ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) ሽልማቱን ባበረከቱበት ወቅት እንደገለጹት፣ የመከላከያ ሠራዊቱ በክልሉ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የከፈለው መስዋዕትነት ከፍተኛ ምስጋና የሚገባው ነው።
ይህ የም
ስጋና መርሃ-ግብር የተካሄደው ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመቐለ ከተማ ተገኝተው ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ሲሆን፣ ከተማ አስተዳደሩም ለጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ የተለያዩ የክብር ስጦታዎችንና ሽልማቶችን አበርክቶላቸዋል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በበኩላቸው፣ የመቐለ ከተማ አስተዳደርና ነዋሪዎች ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበልና ላሳዩዋቸው ፍቅር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
#Ethiopia #ENDF