ቀጥታ፡

በምስራቅ ጉራጌ ዞን ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ምርት በዘመቻ እየተሰበሰበ ነው

ወልቂጤ፣ ሕዳር 4/2019 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሰ ሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ምርት በዘመቻ እየተሰበሰበ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

አርሶ አደሮች በበኩላቸው የተለያዩ የሰው ሃይል አደረጃጀቶችን እና ኮምባይነሮችን ተጠቅመው ምርታቸውን እየሰበሰቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ ሀይሉ ሰይፉ እንደገለጹት የደረሰ ሰብል ወቅቱን ባለጠበቀ ዝናብ ለጉዳት እንዳይዳረገ የሰብል አሰባሰብ ሥራው በዘመቻ እየተከናወነ ነው።

"እኔ እያለሁ አንድም ፍሬ አትባክንም" በሚል መሪ ሃሳብ በዞኑ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ንቅናቄ በማድረግ እየተከናወነ ያለው የምርት አሰባሰብ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል።

በምርት አሰባስብ ሥራው ከአርሶ አደሩ በተጨማሪ በየአካባቢው የተለያዩ የማህበረሰብ አደረጃጀቶች አቀናጅቶ በመጠቀም እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከሰው ሃይል በተጨማሪ ከ78 በላይ የምርት መሰብሰቢያና መውቂያ ኮምባይነሮች የሰብል አሰባሰብ ሥራውን እያቀላጠፉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

እስካሁንም በተለያዩ ሰብሎች ከለማው 73 ሺህ 120 ሄክታር መሬት ውስጥ በ54 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የደረሰ ሰብል መሰብሰቡንም አቶ ሀይሉ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም በቀሪ መሬት ላይ ያለውን የደረሰ ሰብል ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ለመታደግ በዘመቻ የመሰብሰብ ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

ምርታቸውን በዘመቻ እየሰበሰቡ ካሉ የዞኑ አርሶ አደሮች መካከል የመስቃን ወረዳ አርሶ አደር መሃመድ ደድገባ በመኸር ወቅት ያለሙት የጤፍና የበቆሎ ምርት በመድረሱ ከአካባቢያቸው ነዋሪዎች ጋር በጋራ እየሰበሰቡ መሆኑን ተናግረዋል።

የተሰበሰበው ሰብልም ለዝናብ እንዳይጋለጥ መንግስት ባደረገላቸው የመውቂያ ማሽን ድጋፍ ወቅተው ወደ ጎተራ እያስገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በምርት አጨዳና አሰባሰብ ወቅት ሊያጋጥም የሚችለውን የምርት ብክነት ለመቀነስ በየደረጃው ባሉ አመራሮችና ባለሙያዎች ድጋፍ ሲደረግላቸው መቆየቱን የተናገሩት ደግሞ የሶዶ ወረዳ አርሶ አደር ሻወል ወዳጆ ናቸው ።

ይህም በመኸር አዝመራ ያለሙት የጤፍ ምርት ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ሳይጎዳባቸውና ሳይባክን ለመሰብሰብ እንዳስቻላቸው ገልፀዋል። 

በመንግስት ዘመናዊ የመውቂያ ማሽን መቅረቡ ሥራቸውን ለማፋጠን እንዳስቻላቸው ጠቁመው፣ በተደረገላቸው እገዛም መደሰታቸውን ገልጸዋል።

 ፎቶ አለው 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም