የህዝቦችን የአብሮነት እሴት በማጠናከር የጋራ ሰላም እና ልማትን ይበልጥ ማረጋገጥ ይገባል - ኢዜአ አማርኛ
የህዝቦችን የአብሮነት እሴት በማጠናከር የጋራ ሰላም እና ልማትን ይበልጥ ማረጋገጥ ይገባል
አሶሳ፤ ህዳር 05/2019(ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በኦሮሚያ ክልል አጎራባች አካባቢዎች የህዝቦችን የአብሮነት እሴት በማጠናከር የጋራ ሰላም እና ልማትን ይበልጥ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተመለከተ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የኦሮሚያ ክልል አጎራባች አካባቢዎች የጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በአሶሳ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እድሪስ ሙሐመድ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በወንድማማች ሕዝቦች መካከል የቆየውን የአብሮነት እሴት በማጠናከር የጋራ ሰላም እና ልማትን የሚያረጋግጡ ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል።
ሰላም የማይፈልጉ አካላት በህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በማክሸፍ የልማት ሥራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።
የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ደረጀ ባይሳ በበኩላቸው፤ የክልሎቹ ሕዝቦች በባህል እና በታሪክ የተሳሰሩ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ለዘመናት የቆየውን ወንድማማችነት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ተገኝተዋል።