ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ በኮፕ 32 ጉዳዮች በጋራ ይሰራሉ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 4/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ በኮፕ 32 ጉዳዮች በጋራ እንደሚሰሩ ገለጹ።

31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል።

የገንዘብ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን፣ ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ስራ አስፈፃሚ ክሪስቶፍ ለኩርቲየር ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር ያለ አጋርነትን ይበልጥ ለማጠናከር እና በኮፕ 32 ጉዳዮች ላይ ቀጣይነት ባለው መልኩ መስራት ላይ ያተኮረ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም