ቀጥታ፡

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ሞዛምቢክን አሸነፈች

አዲስ አበባ፤ ህዳር 4/2019 (ኢዜአ)፦ በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ ጋር ባደረገው ጨዋታ 1 ለ 0 አሸንፏል።

በዚምፔቶ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ 10 ጨዋታ ከነዓን ማርክነህ በ85ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።

በሁለተኛው አጋማሽ ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን አድርጓል።

በመጀመሪያ አጋማሽ ሞዛምቢክ ያገኘቻቸውን የግብ እድሎች መጠቀም አልቻለችም።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድብ 10 የመጀመሪያ ሶስት ነጥቧን አግኝታለች።

ዋልያዎቹ በሶስት ነጥብ ደረጃዋን ከአራተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጋለች።

ሞዛምቢክ በአምስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

የሁለቱ ሀገራት ቀጣይ የማጣሪያ ጨዋታ ማክሰኞ ህዳር 8 2019 ዓ.ም በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ይካሄዳል።

ሴኔጋል በሰባት ምድቡን እየመራች ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም