ቀጥታ፡

ማንችስተር ዩናይትድ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 4/2019 (ኢዜአ)፦ ማንችስተር ዩናይትድ አርጀንቲናዊውን አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖን በዋና አሰልጣኝነት መሾሙን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የ54 ዓመቱ ፖቸቲኖ የሁለት ዓመት ከስድስት ወር ውል በመፈራረም ቡድኑን ህዳር 9 2019 ዓ.ም ይረከባል።

ክለቡ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው አሰልጣኝ ማይክል ካሪክን ከኃላፊነት ማሰናበቱን ተከትሎ መሆኑን ስካይ ስፖርት ዘግቧል።

የቀድሞው የቶተንሃም እና የቼልሲ አሰልጣኝ የሆነው ፖቸቲኖ፣ በአሁኑ ወቅት ከአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ያለበትን ኃላፊነት ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ኦልድትራፎርድ በማምራት ሥራውን ይጀምራል።

አሰልጣኙ ከአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ጋር በመጪዎቹ የኮንካካፍ ኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች ከሄይቲ ጋር የምታደርገውን ፍልሚያ በመምራት የመጨረሻ ግዴታውን እንደሚወጣ ተገልጿል።

ፖቸቲኖ ማንችስተር ዩናይትድ በሊጉ ከተቀናቃኙ ሊቨርፑል ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ስራውን ይጀምራል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም