የኢትዮጵያና ዩኤንዲፒ የአየር ንብረት እና ዘላቂ ልማት አጋርነት - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያና ዩኤንዲፒ የአየር ንብረት እና ዘላቂ ልማት አጋርነት
አዲስ አበባ፤ ህዳር 4/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) በአየር ንብረት እና በዘላቂ የልማት ስራዎች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ።
31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል።
“ጉዞ ወደ ዘላቂ፣ አይበገሬነት እና ፍትሃዊነት ወደተረጋገጠበት መጻኢ ዘመን” የጉባኤው መሪ ቃል ነው።
የገንዘብ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከጉባኤው ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ዋና ሀላፊ አሌክሳንደር ደ ክሩ ጋር ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ዩኤንዲፒ በአየር ንብረት ፋይናንስ፣ ዘላቂ ልማት፣ በኢንቨስትመንት እና የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅምን በማጎልበት ላይ ያላቸውን የረጅም ጊዜ አጋርነት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያም ሀሳብ ተለዋውጠዋል።