ቀጥታ፡

ዋነኛ ትኩረታችን ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ፣ የሕዝባችንን የመኖሪያ ቤት ጫና ማቃለል እና በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ ቤተሰቦች የተሻለ የኑሮ ምዕራፍ መክፈት ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 4/2019 (ኢዜአ)፦ ዋነኛ ትኩረታችን ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ፣ የሕዝባችንን የመኖሪያ ቤት ጫና ማቃለል እና በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ ቤተሰቦች የተሻለ የኑሮ ምዕራፍ መክፈት የው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአምስት ዓመታት ውስጥ ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ ለሕዝባችን ቃል ገብተናል፤ ይህንንም ቃላችንን በተግባር ለማረጋገጥ ቀን ከሌት ያለ እረፍት እየተጋን እንገኛለን ብለዋል።

ሕዝባችን በመኖሪያ ቤት እጥረት ምክንያት የሚገጥመውን ፈተናና ስጋት በሚገባ እንረዳለን፤ ደረጃቸውን የጠበቁና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ መኖሪያ ቤቶችን ማመቻቸት የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን፣ ለዜጎቻችን ያለብን አደራና ኃላፊነት መሆኑንም ጠንቅቀን እንገነዘባለን ሲሉ ገልጸዋል።

ዋነኛ ትኩረታችን ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ፣ የሕዝባችንን የመኖሪያ ቤት ጫና ማቃለል እና በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ ቤተሰቦች የተሻለ የኑሮ ምዕራፍ መክፈት እንደሆነም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም