ቀጥታ፡

አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ ዛሬ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 4/2019 (ኢዜአ)፦ በሴኔጋል ዳካር ሲካሄድ የቆየው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል።

ሻምፒዮናው ከጥቅምት 21 2019 ዓ.ም አንስቶ ሲካሄድ ቆይቷል።


በውድድሩ ከ204 ሀገራት እና የስደተኞች ኦሊምፒክ ቡድንን ጨምሮ ከ2 ሺህ 650 በላይ ስፖርተኞች ተሳትፈዋል።

ስፖርተኞቹ በ25 የውድድር እና በ10 የተሳትፎ በድምሩ በ35 የስፖርት ዓይነቶች ተሳትፈዋል።

ኢትዮጵያም በአትሌቲክስ፣ ውሹ ውሃ ዋና፣ ብስክሌት እና ቴኳንዶ ስፖርቶች ተሳትፎ አድርጋለች።

በዚህም ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ 5 የወርቅና 3 የብር ሜዳሊያዎችን፣ በድምሩ 8 ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ በዓለም የአትሌቲክስ ሜዳሊያ ሰንጠረዥ አንደኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች።

በውሹ ታዳጊው ናትናኤል ክንፈ የነሐስ ሜዳልያ አግኝቷል።

ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ስፖርቶች አምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ቻይና፣ ጃፓን፣ ሩሲያ እና ግብጽ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

የአራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ የመዝጊያ ስነ ስርዓት በዲያምኒያዲዮ ከተማ በሚገኘው የኦሊምፒክ መንደር ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም