ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ጀርመን ትብብራቸውን ማጠናከር ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 4/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ጀርመን አየር ንብረት ጥበቃን ጨምሮ አጠቃላይ ትብብራቸውን ማጠናከር ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን ከጀርመን የአካባቢ ጥበቃ፣ የአየር ንብረት እርምጃ፣ የተፈጥሮ ጥበቃና ኒውክሌር ደህንነት ፌዴራል ሚኒስቴር ስቴት ሴክሬታሪ ሃይኬ ሄን (ዶ/ር) ጋር የሁከትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

ውይይቱ የኢትዮጵያና የጀርመን ትብብርን ማጎልበት እና ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጥበቃ እርምጃን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም