ማርታ አለማየሁ የዓለም አትሌቲክስ የሴቶች ምርጥ ተስፋኛ አትሌት ሽልማት የመጨረሻ ዕጩ ውስጥ ገባች - ኢዜአ አማርኛ
ማርታ አለማየሁ የዓለም አትሌቲክስ የሴቶች ምርጥ ተስፋኛ አትሌት ሽልማት የመጨረሻ ዕጩ ውስጥ ገባች
አዲስ አበባ፤ ህዳር 3/2019 (ኢዜአ)፦ አትሌት ማርታ አለማየሁ የ2026 የዓለም አትሌቲክስ የሴቶች ምርጥ ተስፋኛ አትሌት ሽልማት የመጨረሻ ሶስት ዕጩ ዝርዝር ውስጥ ገብታለች።
አትሌት ማርታ እ.አ.አ በ2026 ካስመዘገበቻቸው ዋና ዋና ስኬቶች መካከል በአሜሪካ በተካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች (U20) የአገር አቋራጭ ሻምፒዮና በስድስት ኪሎ ሜትር ውድድር ክብሯን በድጋሚ ማስጠበቋ ነው።
በፈረንሳይ ሊል በተካሄደ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ 14 ደቂቃ ከ15 ሴኮንድ በመግባት በዓለም ታሪክ ሶስተኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዘግባለች።
አሜሪካዊቷ የአጭር ርቀት ሯጭ ሚያ ማክስዌል እና ቻይናዊቷ የጦር ውርወራ ስፖርተኛ ያን ዚዪ ሌሎች እጬዎች ናቸው።
አትሌቶቹ ከ20 ዓመት በታች የእድሜ ክልል የሽልማት ዘርፍ የሚገኙ ናቸው።
አትሌት ትዕግስት አሰፋ በዓለም አትሌቲክስ የአዋቂ ሴቶች እጩዎች ዝርዝር አራተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወቃል።
የ2026 የዓለም አትሌቲክስ ምርጥ አትሌቶች የሽልማት ስነ ስርዓት ህዳር 20 2019 ዓ.ም በሞናኮ ይካሄዳል።