ቀጥታ፡

ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩዋንዳ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር በርናዴት አራክዊዬ (ዶ/ር) ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 /2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ ከሩዋንዳ ሪፐብሊክ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር በርናዴት አራክዊዬ ጋር ለCOP32 ዝግጅት ትብብርን ለማጠናከር ሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

ሁለቱ ወገኖች በጋራ ቅድሚያ በተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በቅርበት ለመሥራትና ለሁሉም አካላት ትርጉም ያላቸው ውጤቶችን የሚያስገኝ የተሳካ COP32 እንዲኖር ጥረቶቻቸውን ለማስተባበር ተስማምተዋል።

#COP31 #COP32 #ClimateAction

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም