የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ሽንፈት አስተናገደ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ሽንፈት አስተናገደ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 3/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ከሞሮኮ ጋር ባደረገው ጨዋታ 1 ለ 0 ተሸንፏል።
በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዩኑስ ኤል ባህራዊ በ29ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።
ወጣት ብሔራዊ ቡድኑ በሁለተኛው አጋማሽ ያገኛቸውን ግልጽ የግብ እድሎችን መጠቀም አልቻለም።
የብሔራዊ ቡድኖቹ የመልስ ጨዋታ ህዳር 8 2019 ዓ.ም በሞሮኮ ራባት ይካሄዳል።
በደርሶ መልስ የሚያሸንፈው ሀገር ወደ መጨረሻው ዙር ማጣሪያ ያልፋል።
ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በግብጽ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።
በውድድሩ ላይ ግብጽን ጨምሮ ስምንት ሀገራት ይሳተፋሉ።