ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ቀሪ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 3/2019 (ኢዜአ)፦ የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ቀሪ መርሃ ግብር ዛሬ ይፋ ሆኗል።

በዚህም መሰረት ከ6ኛ እስከ 17ኛ ሳምንት የሚገኙ መርሃ ግብሮች እንዲሁም የ2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ሳምንት ስድስት ተስተካካይ ጨዋታዎች የሚካሄዱበት ጊዜ ታውቋል።

የቀሪው የመጀመሪያ ዙር መነሻ የሆነው የ6ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም. በአዲስ አበባ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየሞች እንደሚጀመር የሊጉ አክሲዮን ማህበር ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም