12ኛው የአፍሪካ ምርት አቅርቦትና ፋሽን ሳምንት (ASFW Addis 2026) በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
12ኛው የአፍሪካ ምርት አቅርቦትና ፋሽን ሳምንት (ASFW Addis 2026) በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፤ህዳር 3/2019(ኢዜአ)፦12ኛው የአፍሪካ ምርት አቅርቦትና ፋሽን ሳምንት (ASFW Addis 2026) በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
የአፍሪካ ትልቁ የጨርቃጨርቅና የቆዳ ውጤቶች ኤግዚቢሽንም በአዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በይፋ ተከፍቷል።
በማስጀመሪያ መርሀግብሩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዳጋቶ ኩምቤ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍጹም ከተማ እንዲሁም የበርካታ ሀገራት የዘርፉ ተዋንያን ተገኝተዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዳጋቶ ኩምቤ ኢትዮጵያ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ከፍተኛ ተጨማሪ እሴት ያላቸው የቆዳና የጨርቃጨርቅ ምርቶች አምራችነት እየተሸጋገረች ነው ብለዋል።
መርሃ ግብሩ የኢንዱስትሪዎችን አቅም ለማሳየት፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስተዋወቅ፣ የንግድ ትብብሮችን ለማጠናከር፣ ልምድ ለመለዋወጥና የኢትዮጵያን ኢንዱስትሪዎች ከዓለም-አቀፍ ገበያዎች ጋር ለማገናኘት ዕድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍጹም ከተማ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማጠናከር በርካታ ተግባራትን ማከናወኗን ገልጸዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን (IPDC) በመላ አገሪቱ የሚገኙ 14 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን እያስተዳደረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ኤግዚቢሽኑ ከዛሬ ጀምሮ አስከ ህዳር 6 ቀን 2019 ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል።