ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና የእስያ ኢንፍራስትራክቸር ኢንቨስትመንት ባንክ የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የእስያ ኢንፍራስትራክቸር ኢንቨስትመንት ባንክ የአጋርነት ስራዎችን ለማስቀጠል ያለመ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል።

“ጉዞ ወደ ዘላቂ፣ አይበገሬነት እና ፍትሃዊነት ወደተረጋገጠበት መጻኢ ዘመን” የጉባኤው መሪ ቃል ነው።


 

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን ከእስያ ኢንፍራስትራክቸር ኢንቨስትመንት ባንክ(AIIB) ፕሬዝደንት ዞ ጂያይ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ የአጋርነት ስራዎችን ለማስቀጠል ያለመ ነው።

ከአሁን በፊት ተጀምሮ የነበረው የቢሾፍቱ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ፋይናንስ ለማድረግ የነበረውን ውይይት ለመቀጠል ፣ የረጅም ጊዜ አብሮ የመስራት እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን ለመቅረፅ መክረዋል።

እንዲሁም በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የሚካሄደውን ኮፕ 32 መደገፍፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ውይይት አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም