ቀጥታ፡

በዞኑ ቆቦ ጊራና ሸለቆ በኤልኒኖ ክስተት ምክንያት የታጣውን ምርት በመስኖ ለማካካስ የዘር ሥራ እየተከናወነ ነው

ባህር ዳር፣ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፡- በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ጊራና ሸለቆ በኤልኒኖ ክስተት ምክንያት የታጣውን ምርት በመስኖ ለማካካስ የዘር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የቆቦ ጊራና ሸለቆ ልማት ፕሮግራም ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በጽሕፈት ቤቱ የሆርቲካልቸር ልማት ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር አቶ አንዳርጌ አስማረ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በኤልኒኖ ክስተት ምክንያት በመኸር ወቅት የታጣውን ምርት በመስኖ ልማት ለማካካስ እየተሠራ ነው።

ለዚህም በዘንድሮው የበጋ ወቅት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያው ዙር መስኖ 2 ሺህ 89 ሄክታር መሬት በቆቦ ጊራና ሸለቆ በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት ግብ ተይዞ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል።

በመስኖ ልማቱ ስንዴ፣ ሽንብራ፣ በቆሎና ሽንኩርት ለማልማት የዘር ሥራ እየተከናወነ ሲሆን፣ እስካሁን በተደረገው እንቅስቃሴ 242 ሄክታር በዘር መሸፈን ተችሏል ብለዋል።

በሁለተኛው ዙር መስኖ ልማት ደግሞ 819 ሄክታር መሬት የሚለማ ሲሆን፣ በልማቱ 2 ሺህ 976 አርሶ አደሮች በአንደኛና በሁለተኛ ዙር ከሚያለሙት መሬት 174 ሺህ 965 ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

ምርታማነትን ለማሳደግም አርሶ አደሮች በቂ ግብዓት እንዲጠቀሙ ለማድረግ የባለሙያ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን የቆቦ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ኩርፋ መንገሻ እንዳሉት፣ አንድ ሄክታር በሚጠጋ መሬት ላይ ሰብል በመስኖ የማልማት ሥራ እያከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

"በአካባቢው ባጋጠመው ድርቅ ምክንያት በመኸር ወቅት ያጣሁትን ምርት በመስኖ ልማት በማካካስ፣ ከራሴ የምግብ ፍጆታ የተረፈ ምርት አምርቼ ለገበያ ለማቅረብ እየሠራሁ እገኛለሁ" ብለዋል።

በቆቦ ጊራና ሸለቆ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት ታግዘው ባለፈው ዓመት ለአንድ ሄክታር ሩብ የቀረው መሬታቸውን በበጋ ስንዴ አልምተው 25 ኩንታል ምርት እንዳገኙ የገለጹት ደግሞ የዚሁ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ተስፋው አማረ ናቸው።

በዘንድሮው የበጋ ወቅትም ስንዴና ማሾ ለማልማት የእርሻ ዝግጅት ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም