ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቦትስዋናው ፕሬዝዳንት ዱማ ጌዲዮን ቦኮ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቦትስዋናው ፕሬዝዳንት ዱማ ጌዲዮን ቦኮ ተወያዩ
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቦትስዋናው ፕሬዝዳንት ዱማ ጌዲዮን ቦኮ ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ወቅት ከቦትስዋናው ፕሬዝዳንት ዱማ ጌዲዮን ቦኮ ጋር ተወያይተናል ብለዋል።
በውይይታችንም ሁለቱ ሀገሮች የተጋረጡባቸውን የጋራ የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችና እየወሰድናቸው ያሉትን ምላሾች ጨምሮ በCOP32 ላይ ትብብራችንን ለማጠናከር፣ ጠንካራ የአፍሪካ አየር ንብረት አጀንዳን ወደፊት ማስቀጠል እንዲሁም በሌሎች ሰፊ የሁለትዮሽ ትብብር መስኮች ላይ መክረናል ብለዋል።