ቀጥታ፡

ለዛሬውና ለመጪው ትውልድ የተሻለችና ዘላቂ ከተማ ለመገንባት በቁርጠኝነት እንሠራለን - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፦ ዘላቂ፣ አረንጓዴና አካታች የከተማ ልማትን ለማረጋገጥ ያለንን ትብብር ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር ለዛሬውና ለመጪው ትውልድ የተሻለችና ዘላቂ ከተማ ለመገንባት በቁርጠኝነት እንሠራለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ከCOP31 መድረክ ጎን ለጎን፣ ከህፃናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኬት ሃምፕተን ጋር ገንቢ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

ከዋና ሥራ አስፈጻሚ ሃምፕተን ጋር ኢትዮጵያ የCOP32 አዘጋጅ ሀገር እንደመሆኗ በትብብር ዕድሎች፣ እንዲሁም በቆሻሻ አያያዝና አጠቃቀም ፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋምና የከተሞች ትብብርን በማጠናከር ዙሪያ መወያየታቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከንቲባዋ ዘላቂ፣ አረንጓዴና አካታች የከተማ ልማትን ለማረጋገጥ ያለንን ትብብር ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር ለዛሬውና ለመጪው ትውልድ የተሻለችና ዘላቂ ከተማ ለመገንባት በቁርጠኝነት እንሠራለን ብለዋል

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም