ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል-ታኒ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፦  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል-ታኒ ጋር ውይይት አካሂደዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል-ታኒ ጋር ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።



 
ውይይቱ የረጅም ጊዜ ግንኙነታችንን ይበልጥ ለማጠናከር እና የጋራ የመልማት አቅም ባላቸው ዘርፎች ላይ ያለንን ትብብር ለማሳደግ ያለመ ነበር ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም