ቀጥታ፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ ከአፍሪካ የድርድር ቡድን (AGN) ሊቀመንበር ዶ/ር አንትዊ-ቦአሲያኮ አሞአ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፦ በCOP31 አንታሊያ ከሚካሄዱ ዝግጅቶች ጎን ለጎን፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ ከአፍሪካ የድርድር ቡድን (AGN) ሊቀመንበር ዶ/ር አንትዊ-ቦአሲያኮ አሞአ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

ውይይቱ ለአፍሪካ ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ማለትም የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ (adaptation)፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ፣ ፍትሐዊ ሽግግር (just transition) እና ትግበራን ላይ ያተኮረ እንደሆነም ተገልጿል።


 

በተጨማሪም፣ ታዳጊ ሀገሮች በብሔራዊ የተወሰኑ አስተዋጽኦዎቻቸው (NDCs) እና በብሔራዊ የማጣጣሚያ ዕቅዶቻቸው (NAPs) ትግበራ የበለጠ ድጋፍ እንዲያገኙ እንዲሁም የአየር ንብረት እርምጃዎች የአፍሪካን የልማት ቅድሚያዎች እንዲመልሱ አስፈላጊነቱን በተመለከተም መወያየታቸው ተመላክቷል።

የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንቱ ለCOP32 ዝግጅቶች እየተጠናከሩ በሚሄዱበት ወቅት ኢትዮጵያ ከAGN ጋር የቅርብ ምክክር እንደምታደርግ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በአንታልያ የተሳካ ውጤት ማስመዝገብ፣ በድርድሩ ሂደቱ ላይ ያለውን እምነት ማጠናከር እና ከቃል ኪዳኖች ወደ ተግባራዊ አፈጻጸም መሸጋገር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቅድሚያዎችና አመለካከቶች (Africa’s priorities and perspectives) ወደ COP32 በሚደረጉ ዝግጅቶችና ውይይቶች ሂደት በጥንካሬ እንዲንጸባረቁ ከAGN ጋር በቅርበት መሥራቷን ትቀጥላለች ነው ያሉት።

#COP31 #COP32 #AfricaForClimate

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም