ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር ውይይት አካሂደዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
በውይይታችንም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ያለውን ትብብር ማሳደግ፣ በኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ማበረታታት እና ኖርዌይ ኢትዮጵያ ለምትረከበው የCOP32 ፕሬዝዳንትነት የምታደርገውን ድጋፍ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ መምከራቸውን አመልክተዋል።
ውይይታችን ሰፊ የሁለትዮሽ ትብብርን ጨምሮ በወቅታዊ፣ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሃሳብ ልውውጥ የተደረገበት ነው ብለዋል።
ይህም በተግባራዊ የትብብር መስኮች ወደፊት ለመራመድና አጋርነታችንን ይበልጥ ለማጠናከር ያለንን የጋራ ፍላጎት ያንጸባረቀ ሲሉ ገልጸዋል።