ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ክህሎት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ቁርጠኝነቷን ገለጸች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ክህሎት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ቁርጠኝነቷን ገለጸች
አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በኮፕ-31 ጎን ለጎን በተካሄደ የውይይት መድረክ የአረንጓዴ ክህሎት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ቁርጠኝነቷን ገለጸች
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኮፕ-31 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደው "ዝቅተኛ የካርቦን ኢኮኖሚን ለመገንባት ክህሎትን ማሳደግ እና የሥራ ዕድል ፈጠራን ማፋጠን" በተሰኘ መድረክ ላይ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ክህሎት ልማት ላይ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትሩ አቶ በረከት ፍስሃጽዮን እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በሰው ሀብት ልማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ የወጣቶችን የሥራ ዕድል ለማስፋፋት እና ፍትሐዊ የሆነ አረንጓዴ የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራች ትገኛለች።
አዲሷን አስተናጋጅ አዲስ አበባን ለኮፕ-32 ጉባኤ ዝግጁ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት፣ የታዳሽ ኃይል ማፋጠን እና የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ለወጣቶች በርካታ የሥራ ዕድሎችን እንደፈጠሩ እና አሁንም አዳዲስ አጋጣሚዎችን እየከፈቱ መሆናቸውን ሚኒስትሩ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።