ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ ለኮፕ 32 ዝግጅት ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ያላቸውን የጋራ ፍላጎታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 1/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ ለኮፕ 32 ዝግጅት ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ።

31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል።

“ጉዞ ወደ ዘላቂ፣ አይበገሬነት እና ፍትሃዊነት ወደተረጋገጠበት መጻኢ ዘመን” የጉባኤው መሪ ቃል ነው።

የገንዘብ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን ከኖርዌይ የአየር ንብረትና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ሲግሩን ጄርሎው አስላንድ ጋር ተወያይተዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች በተለይም ለኮፕ 32 ዝግጅት ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ያላቸውን የጋራ ፍላጎት ገልጸዋል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሥር የሚከናወኑ የደን ልማት ጥረቶችን ማስፋፋት እና ለአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ያላቸውን አስተዋጽኦ ማጉላት ያለውን አስፈላጊነትም ተነጋግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም