ቀጥታ፡

የኮሪደር ልማት የአካል ጉዳተኞችን ፍላጎት ያገናዘበና ሁለገብ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ነው

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 1/2019 (ኢዜአ) ፦በከተሞች እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት  የአካል ጉዳተኞችን ፍላጎት ያገናዘበና ሁለገብ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ መሆኑን  የተለያዩ የስፖርት ዘርፍ አመራሮች ገለፁ።

በመደመር መንግሥት እይታ በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት የአፍሪካ መዲናዋን ሁለንተናዊ ገጽታ በመቀየር ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ አድርጓል።

በዓይነቱ ልዩ የሆነው ይህ አጠቃላይ የልማት እንቅስቃሴ ከአዲስ አበባ ባለፈ በሁሉም የክልል ከተሞች ተስፋፍቷል።

እነዚህ ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴዎች ኢትዮጵያ በተለያዩ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መስኮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ ሀገር እንድትሆን አስችለዋታል።

የኢትዮጵያ ዊልቸር ቅርጫት ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አባይነህ ጉጆ ለኢዜአ እንዳሉት፣ በሀገሪቱ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለአካል ጉዳተኞች ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ናቸው።

የኮሪደር ልማት ገና ከጅምሩ የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ያካተተ በመሆኑ፣ የእግረኛ መንገዶች፣ ማረፊያዎች፣ መናፈሻዎች እና መጸዳጃ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ምቹ ሆኖ እንዲሆኑ አስችሏል።

ቀደም ሲል በነበሩት የመሠረተ ልማት አካታችነት ችግር ምክንያት አካል ጉዳተኞች እንግልት ይደርስባቸው እንደነበርም አስታውሰዋል።

የአሁኑ የልማት እንቅስቃሴ ይህንን ችግር በመቅረፍ የህብረተሰቡን አካታችነት በተግባር ያረጋገጠ በመሆኑ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ይህም የዜጎችን እኩል ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ለቀጣይ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች አርአያ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ የቦርድ አባል እና አቃቢነዋይ አቶ ጥላሁን ጀማነህ በበኩላቸው፣ በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማዋን የቀድሞ ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ አሻሽሏል።

ልማቱ ቀደም ሲል በግንባታዎች ወቅት ትኩረት አጥተው የተዘነጉ አበይት ጉዳዮችን ባካተተ መልኩ በአስደናቂ ሁኔታ መከናወኑንም አብራርተዋል።

በተለይም መሰረተ ልማቶቹ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ እና የሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍል ፍላጎት ያገናዘቡ  ሆነው መገንባታቸውን አድንቀዋል።

በመሆኑም ይህ አካታች የልማት ሥራ ኢትዮጵያ ወደፊት ለሚካሄዱ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በአስተማማኝ ሁኔታ ተመራጭ እንድትሆን ትልቅ በር የከፈተ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም