ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የሜትሮሎጂ ድርጅት የአየር ንብረት ጥበቃና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ትብብራቸውን ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የሜትሮሎጂ ድርጅት የአየር ንብረት ጥበቃና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ትብብራቸውን ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 1/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የሜትሮሎጂ ድርጅት የአየር ንብረት ጥበቃና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ትብብራቸውን የበለጠ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።
31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል።
“ጉዞ ወደ ዘላቂ፣ አይበገሬነት እና ፍትሃዊነት ወደተረጋገጠበት መጻኢ ዘመን” የጉባኤው መሪ ቃል ነው።
በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች።
የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር በረከት ፍስሃፅዮን ከጉባኤው ጎን ለጎን ከዓለም አቀፉ የሜትሮሎጂ ድርጅት (WMO) ዋና ጸሐፊ ፕሮፌሰር ሴሌስቴ ሳውሎ ጋር ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ በአየር ንብረትና የአየር ሁኔታ ምልከታ ሥርዓቶች ላይ ያለውን ትብብር ማጠናከር፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ አቅሞችን ማሳደግ፣ የአየር ንብረት መረጃዎችን ፍትሃዊ ተደራሽነት ማበረታታት እና በአዲስ አበባ ከሚካሄደው ኮፕ 32 በፊት በሳይንስ ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ጥበቃን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው።
ውይይቱ በጠንካራ የምልከታ አውታረ መረቦች፣ በመረጃ ፍትሃዊነት፣ በአቅም ግንባታ እና በዓለም አቀፍ ትብብር አማካኝነት የመቋቋም አቅምን ለማጠናከር ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጧል።