በሐረር ከተማ በግብርና ኢንቨስትመንት የተከናወኑ የልማት ስራዎች ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገሩ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
በሐረር ከተማ በግብርና ኢንቨስትመንት የተከናወኑ የልማት ስራዎች ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገሩ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 1/2019 (ኢዜአ)፦ በሐረር ከተማ በግብርና ኢንቨስትመንት የተከናወኑ የልማት ስራዎች ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገሩ እንደሚገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ በአነስተኛ መነሻ ካፒታል የተጀመሩ ኢንቨስትመንቶች በጥቂት ዓመታት ውስጥ የካፒታል አቅማቸውን ማሳደግ መቻሉን አመልክተዋል።
የድለባ ጊዜያቸውን የጨረሱ የሐረር ሠንጋዎችን፣ በየሶስት ወሩ ለውጭ ገበያ በማቅረብም የውጭ ምንዛሬ ግኝት እንዲጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በቀጣይም በዚህ ዘርፍ በሰፊው በመሰማራት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እና የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ በሚደረገው ሂደት ውስጥ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በትጋት እንዲሰሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።