ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከኪሳራና ጉዳት ምላሽ ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ኢብራሂማ ቼይክ ዲዮንግ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከኪሳራና ጉዳት ምላሽ ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ኢብራሂማ ቼይክ ዲዮንግ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2019 (ኢዜአ)፦ የገንዘብ ሚኒስትር እና ና የኮፕ 32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን ከኪሳራና ጉዳት ምላሽ ፈንድ (FRLD) ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ኢብራሂማ ቼይክ ዲዮንግ ጋር በኢትዮጵያ ፓቪሊዮን የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) ዛሬ በቱርኪዬ አንታሊያ መካሄድ ጀምሯል።
የገንዘብ ሚኒስትር እና ና የኮፕ 32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን ከኪሳራና ጉዳት ምላሽ ፈንድ (FRLD) ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ኢብራሂማ ቼይክ ዲዮንግ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
ውይይታቸው በጋራ የአየር ንብረትና የዘላቂ ልማት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ዙሪያ ትብብርን በማጠናከርና አዳዲስ የጋራ የሥራ ዕድሎችን ማፈላለግ ላይ ያተኮረ ነው።
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከሚካሄደው ኮፕ 32 በፊት አጋርነትን ለማጠናከርና የጋራ ጥረቶችን ለማስቀጠል ሐሳብ ተለዋውጠዋል።