ቀጥታ፡

ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከፒ ፎር ጂ (P4G) ዋና ዳይሬክተር ሮቢን ማክጉኪን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ጥቅምት 30፣ 2019 ዓ.ም (ኢዜአ)የገንዘብ ሚኒስትርና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከP4G (Partnering for Green Growth and the Global Goals) ዋና ዳይሬክተር ሮቢን ማክጉኪን ጋር ውይይት አካሄዱ።

በውይይታቸውም የአየር ንብረት ፈጠራ ሥርዓቶችን ማጠናከር፣ ለአየር ንብረት ጉዳይ ሥራ ፈጣሪዎች የሚደረገውን ኢንቨስትመንት ማሳደግ፣ እንዲሁም ለዘላቂ ልማትና ለአረንጓዴ ዕድገት የሚያግዙ ተግባራዊ መፍትሔዎችን ማስፋፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ሐሳብ ተለዋውጠዋል።

በተጨማሪም በየካቲት 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄደው የP4G ኢትዮጵያ ጉባኤ፣ ወደ COP32 በሚደረገው ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን አጉልተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም