ቀጥታ፡

ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የኃይል ኤጀንሲ (IEA) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፋቲህ ቢሮል ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 30/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣  በቱርክዬ አንታሊያ በመካሄድ ላይ ካለው COP31 ጎን ለጎን ከዓለም አቀፉ የኃይል ኤጀንሲ (IEA) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፋቲህ ቢሮል ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለውንና ዘላቂ የኃይል ተደራሽነትን ማስፋፋት፣ በንጹህ ኃይል ልማት ላይ ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል ።

 እንዲሁም የአፍሪካን እያደገ የሚሄድ የኃይል ፍላጎትና የልማት ግቦች ለመደገፍ ኢንቨስትመንትን ማሳደግ እና የካፒታል ከፍተኛ ወጪን መቅረፍ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል።

ሁለቱ ወገኖች በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከሚካሄደው COP32 በፊት ሊኖሩ ስለሚችሉ የትብብር ዕድሎች ሐሳብ በመለዋወጥ፣ የኃይል ተደራሽነትን፣ ዘላቂ ልማትንና የአየር ንብረት እርምጃን ተያያዥና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።

#COP31 #COP32Ethiopia #EnergyAccess #ClimateAction

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም