ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30 /2019 (ኢዜአ)፦ አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች በሴኔጋል ዳካር መካሄዱን ቀጥሏል።

ማምሻውን በተካሄደ የ1500 ሜትር ወንዶች ፍጻሜ አትሌት ዋቢ ወጂራ አሸንፏል።

3 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ73 ማይክሮ ሴኮንድ አትሌቱ የገባበት ጊዜ ነው።

በዚህም ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።

ዛሬ በተካሄደ የ2000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ፍጻሜ አትሌት ጁነዲን አብዶ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም