ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30 /2019 (ኢዜአ)፦ አትሌት ጁነዲን አብዶ ለኢትዮጵያ በአራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

የወጣቶች ኦሊምፒክ ከጥቅምት 21/ 2019 ዓ.ም አንስቶ በሴኔጋል ዳካር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።

በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያ እየተሳተፈች ትገኛለች።


 

ዛሬ በተካሄደው በ2000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ፍጻሜ በ5 ደቂቃ ከ29 ሰከንድ ከ30 ማይክሮ ሰከንድ አሸናፊ ሆኗል።

ይህም ኢትዮጵያ በውድድሩ ያገኘችው የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳሊያ ሆኖ ተመዝግቧል።

ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ፣ ውሃ ዋና፣ ብስክሌት፣ ወርልድ ቴኳንዶ እና ውሹ ስፖርቶች እየተሳተፈች ትገኛለች።

አራተኛው የወጣቶች የኦሊምፒክ ጨዋታዎች እስከ ህዳር 4 2019 ዓ.ም ይቆያል።

የወጣቶች ኦሊምፒክ በአፍሪካ ምድር ሲካሄድ የሴኔጋሉ የመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም